You can reach our office at anytime at eotcdcp.assn@gmail.com
April 25, 2024 from 9:00 am
በሃገራችን ኢትዮጵያ በየእለቱ የምንሰማው እጅግ ዘግናኝ እና ኢሰብዓዊ ድርጊቶች እረፍት የነሳቸው ኢትዮጵያውያን፤ እንዲሁም የካህናት እና ምዕመናን ሕብረት በሰሜን አሜሪካ ሕዝባዊ ማዕበል በሚል የተጠራውን ሰልፍ ከዋሺንግተን ዲሲ ካፒቶል ሂል እስከ ስቴት ዲፓርትመን የሚዘልቅ ሰልፍ በአፕሪል 25 ሐሙስ ቀን ከጠዋቱ 9፡30 ጀምሮ አዘጋጅቷል፤
ኑ ለወገኖቻችን ድምጽ እንሁናቸው ለአለም አቀፍ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ነባራዊ የሆነ እውነታ እናሳውቅ የአሜሪካን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት እና የስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ ጉዳይ ሃላፊዎችንም በደብዳቤ ጥያቄያችንን እናቀርባለን፤ በዚህ ታሪካዊ የሆነ ሰልፍ ላይ እንደማይቀሩ ተስፋ እናደርጋለን።
አስታውሱ ከጠዋቱ 9፡30 ላይ በካፒቶል ሂል እንገናኝ።
March 31, 2024 from 2:00 pm
ለመላዊ ኢትዮጵያውያን ሰላም ወዳድ ሕዝብ በሙሉ
ኢትዮጵያ ሃገራችን ላለፉት 6 ዓመታት በተለየ ሁኔታ በርካታ ንፁሐን የሚገደሉባት፣ አዛውንት አባት እናቶች የሚታረዱባት፣ ካሕናት አባቶች በቤተመቅደስ የሚገደሉባት፣ ሰላማዊው ወገናችን በሰላም እንዳይኖር የተከለከለበት ጊዜ እንደሆነ ሁላችንም የምንረዳው ሃቅ ነው፤ በመሆኑም የዋሺንግተን ዲሲ የተቋቋመው የካህናት እና ምዕመናን ሕብረት ሰላማዊ ሰልፍ በዋይት ሀውስ ለማርች 31 አዘጋጅቷል እርስዎም እሑድ በመጻጉዕ ሰንበት በዋይት ሃውስ ከ2፡00 ፒኤም ጀምሮ እንድንገናኝ እና ለንጹሐን ወገኖቻችን ድምጻችንን እንድናሰማ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
May 1, 2023 11:23 am.
በመጪው ቅዳሜ ሚያዚያ ፳፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓም በታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት ሊቀ ማምዕራን ፋንታሁን ሙጬ በመንበረ ፓትርያሪክ የቤተክርስቲያን የቴሌቪዥን ማሰራጫ EOTCTV ዋና የበላይ ሃላፊ የሆኑት አባት በቦታው ይገኛሉ፤
ቅድስት ቤተክርስቲያን ያለችበትን አሁናዊ ሁኔታ እና የመንግሥት ተጽዕኖዎች ያስቃኙናል፤ የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም በጋራ እንመክራለን፤
አስታውሱ በመጪው የቅዳሜ ከሰዓት በኃላ በ2፡00 PM ቀጠሯችሁን ከእኛ ጋር እንድታደርጉ እንጋብዛለን፤ ያተርፉበታል ለወዳጅ ለዘመድ በማድረስ ቢተባበሩን በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።
ተጨማሪ መረጃዎች ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር (202) 983᎑842 የደውሉ አድራሻው
በደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ዋሺንግተን ዲሲ
2601 Evarts Street, NE. Washington, DC 20018
በ2፡00 PM መርኅግብሩ በጸሎት ይጀመራል፤ አስታውሱ አይርሱ!
April 13, 2023 8:34 pm
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ፤ በመጪው ሚያዚያ ፳፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓም (May 6, 2023) ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የካህናት እና የምዕመናን ኅብረት በአይነቱ ለየት ያለ የውይይት እንዲሁም የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል፤ በወቅታዊ የሃገራችን ኢትዮጵያ ብሎም በቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሱ ያሉትን ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎችን ለመጠቆም
ጥናታዊ ጽሁፎች በሳል ትችቶች ይቀርባሉ፤
ምሁራን ከኢትዮጵያ ማብራሪያ ይሰጣሉ፤
የምዕመናን ውይይት እና ምክክር ይደረጋል፤
እንዳያመልጥዎት እሑድን ሚያዚያ ፳፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓም (May 6, 2023) ከወዲሁ ቀጠሮዎትን ይያዙ ይደሰቱበታል፤ አንድ ቁምነገር ይጨብጡበታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
አዘጋጅ፡ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የካህናት እና የምዕመናን ኅብረት
ቦታውን በቅርቡ እናሳውቃለን ይጠብቁን
በመጪው ሐሙስ መጋቢት ፳፩ ቀን የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው የካህናት እና የምዕመናን ኅብረት ከኢትዮጵያ ሁለት ትልልቅ የቤተክርስቲያናችንን መምህራንን ጋብዞ ዝግጅቱን አጠናቆ ይጠብቃችኃል፤ አስታውሱ ሐሙስ መጋቢት ፳፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓም ከምሽቱ ፰ ሰዓት ጀምሮ በዙም ይጠብቃችኃል፤ በተለይ ለካህናት እና አገልጋይ አባቶች ዲያቆናት መነኮሳት በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም በታላቅ አክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ተጋባዥ መምህራን ከኢትዮጵያ በቀጥታ የሚገቡት
✥ መሪጌታ ባሕረ ጥበብ ሙጬ
✥ መምህር ፋንታሁን ዋቄ
✥ እንዲሁም የኅብረቱ ሰብሳቢ የሆኑት ርዕሰ ሊቃናት አብርሃም ሀብተ ሥላሴ
From 8:00 pm EST.
Meeting Number: 842 7436 1850
Passcode: 03242023
በመጪው አርብ መጋቢት ፲፭ ቀን የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው የካህናት እና የምዕመናን ኅብረት ከኢትዮጵያ ሁለት ትልልቅ የቤተክርስቲያናችንን መምህራንን ጋብዞ ዝግጅቱን አጠናቆ ይጠብቃችኃል፤ አስታውሱ አርብ መጋቢት ፲፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓም ከምሽቱ ፰ ሰዓት ጀምሮ በዙም ይጠብቃችኃል፤ በተለይ ለካህናት እና አገልጋይ አባቶች ዲያቆናት መነኮሳት በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም በታላቅ አክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ተጋባዥ መምህራን ከኢትዮጵያ በቀጥታ የሚገቡት
✥ መሪጌታ ባሕረ ጥበብ ሙጬ
✥ መምህር ፋንታሁን ዋቄ
✥ እንዲሁም የኅብረቱ ሰብሳቢ የሆኑት ርዕሰ ሊቃናት አብርሃም ሀብተ ሥላሴ
From 8:00 pm EST.
Meeting Number: 842 7436 1850
Passcode: 03242023